ለመጠጥ ውሃ፣ ሳኒቴሽንና ኃይጂን ብሔራዊ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል 60 ሚሊዮን ዩኒት ኦፍ አካውንት (ስልሳ ሚሊዮን ዩኒት ኦፍ አካውንት) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.ኤ.አ ኖቬምበር 28 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ደሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጃል፡፡
•
•