ለአፍሪካ የንግድ ኢንሹራንስ ኤጀንሲ የአባልነት ክፍያ የሚውል መጠኑ 4 ሚሊዮን 970 ሺ ዩ.ኤ( አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰባ ሺ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 30 ቀን 2015 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 27 ቀን 2008 ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው በመሆኑ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦
•
•