ለምስራቃዊና ደቡባዊ አፍሪካ የከፍተኛ ትምህርት የልህቀት ማዕከላት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 17 ሚሊዮን 400 ሺ ኤስ.ዲ.አር (አስራ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኝ የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ባደረገው ስብስባ ያፀደቀው በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦
•
•
•
•
•
•