ከኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሠረታዊ ዓላማዎች አንዱ የሆነውን በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማኅበረሰብ በጋራ የመገንባት ዓላማ ከግብ የሚደርሰው የግለሰብ፣ የብሔር/ብሔረሰብ እና የሕዝብ መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች መከበራቸው ሲረጋገጥ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መስፈን እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገቱ መደራጀት ባካሔደው ረጅም ትግል በከፈለው መስዋዕትነት ሰብአዊ መብቶች ለማናቸውም ዓይነት የተፅዕኖ መዳፍ ሳይጋለጡ በእውን የሚከበሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት የሕዝቦች መብቶችና ነፃነቶች የተከበሩ መሆናቸው በመረጋገጡና በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌደራልና የክልል መንግሥታት አካላትና ባለሥልጣኖቻቸው እነዚህን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነትና ግዴታም እንዳለባቸው በመደንገጉ፤
መብቶቹንና ነፃነቶቹን በማስከበሩ ረገድ የላቀ ድርሻ ይኖራቸዋል ከሚባሉት አካላት አንዱ የሆነውን የሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ማቋቋምና ሥልጣኑንና ተግባሩንም ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር በሚስማማ መልክ በሕግ መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (14) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•