የፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማቀድ፣ የተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ዜጎች ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እና በፍትሕ አስተዳደር ቀልጣፋና ውጤታማ አሠራር እንዲኖር ለማስቻል የሲቪል ምዝገባ እና የቤተሰብ ምዝገባ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ፤
ዜጎች ወሳኝ ኩነቶችን በአግባቡና በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ተደራሽ፣ ሁለን አቀፍ እና አስገዲጅ የሆነ የሲቪል ምዝገባ እና የቤተሰብ ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የብሔራዊ ጥቅምንና ደኅንነትን ለማስጠበቅ እና በመንግሥትና በግል ዘርፍ ለዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ለማድረግ የሲቪል ምዝገባ እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 760/2004 (እንደተሻሻለው) የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት የማያስችል በመሆኑ አዋጁን እንደገና ማውጣት አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐበሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዐስ አንቀፅ (1) እና (6) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•