የመንግሥት ሠራተኞች የሰው ኃይል ምልመላና መምረጣ ግልጽነት ባለው ውድድርና ብታት ላይ እንዲመሠረት፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ኃላፊነት፣ ተግባርና ተልዕኮ በብቃት፣
በጥራትና በሙታማነት እንዲወጡ ለማድረግ፤ ዘመናዊ የሆኑ የአመራር ሥርዓት በመከተል ቀልጣፋ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓት በሕን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ኢትዮጵያን የሚመስል – የመንግሥት ሠራተኞች ስብጥር ማለትም ብዝኃነት እና አካታችነትን ያገናዘበ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት መገንባት ጠቃሚ በመሆኑ፤
የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓትን መዘርጋት፤ በመንግሥት መሥሪያ ቤት የሚሰጡ አገልግስቶችን ለማዘመን፤ የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ሥራን ለማሻሻል፤
ምርታማነት ለመስመርና ለማጎልበት፤ ቤታት ያላቸውን ባለሙያዎች ለማግኘት እና በሥራ ላይ ያሉትንም ለማቆየት ወሳኝ ሆኖ በመገኘቱ፤
የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደርና አደረጃጀት ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ ፍላጎትና
ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል፤ የመንግሥትን የመፈፀም ብቃት በማጎልበት የዜጎችን ፍላጎት የሚያረካ እና ወደ ተሻለ የአድገት ደረጃ ሊያሸጋግር የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በሠራተኞች መካከል ጤናማ ተወዳዳሪነት ለመፍጠር የሚያስችል የማትጊያ እና የማበረታቻ ሥርዓት መርጋት በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 መሠረት የሚኩሴው ታውጇል።
•
•
•
•
•