8ሺ 863 ግራም የኮኬይን እፅ ይዞ የተገኘው ናይጄሪያዊ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

Nigerian National Found in Possession of 8,863 Grams of Cocaine Sentenced to Rigorous Imprisonment

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ 8ሺ 863 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደገኛ እፅ በሻንጣው ውስጥ ደብቆ ይዞ የተገኘው ናይጀሪያዊ ዜጋ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ቅጣት እንዲጣልበት ማድረግ ችሏል፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ሚስተር አኒቡቺ ጁዲ የተባለው ናይጀሪያዊ ዜግነት ያለው ተከሳሽ እፆችን የማምረት፣ የመሥራት የማዘዋወር ወይም የመጠቀም ልዩ ፈቃድ ሳይኖረው ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ሲሆን መነሻውን ከብራዚል ሳኦፖል ከተማ በማድረግ ወደ ጊኒ ኮናክሪ ከተማ ለመጓዝ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ለትራንዚት ባረፈበት ወቅት በተደረገ ኤክስሬይ ፍተሻ 12 እሽግ ኮኬይን ወይም 8ሺ 863. 11 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደገኛ እፅ በሻንጣው ውስጥ ደብቆ ይዞ ሲጓዝ የተገኘ ሲሆን ሰዎችን ሱስ በማስያዝ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እንዲሆኑ ስለሚገፋፋ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወርና በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን የኮኬይን እፅ ፈቃድ ሳይኖረው ይዞ የተገኘ በመሆኑ በፈፀመው አደገኛ እፆችን ማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሽም ክሱ ተነቦለት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ ያለ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግም ተከሳሹ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት እንደ ክሱ ሙሉ በሙሉ ያመነ በመሆኑ ባመነው መሠረት በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ይሰጥልኝ ሲል አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር በዝርዝር ያመነ በመሆኑ ባመነው መሠረት ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተውም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ወንጀል ችሎትም ተከሳሽን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል ያለውን በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡

Tagged Under: 000 birr fine • 20 • airlines • airport • bole • bole international airport • cocaine • cocaine trafficking • Criminal Conviction • drug • drug smuggling • Ethiopian Airlines • Federal High Court • illicit drug trade • international • international drug trafficking • nigeria • paulo • Rigorous Imprisonment • sao • sao paulo • Smuggling • trafficking
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች