ዮሲያድ አበጀ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ የተደራጁ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጄኔራልን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡ በእርሱ አመራር የስራ ክፍሉ በሕገመንግሥት እና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የሕዝቦች ደህንነት እና ሰላማዊ ህይወት ላይ የሚቃጣ ጥቃት፣ የሽብር ወንጀሎችን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮችን ምርመራ ማስተባበር እና ስኬታማ ክርክር ማድረግ ተችሏል፡፡ የሥራ ክፍሉ ዉጤታማ መሆን እንዲችል ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ አቶ ዮሲያድ የሞያ ሥራቸዉን የጀመሩት በፍትሕ ሚኒስቴር ዐቃቤ ሕግ ሆነዉ በማገልገል ሲሆን ከሰኔ 2008 እስከ የካቲት 2012 ዓ.ም በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነዉ አገልግለዋል፡፡ ከዳኝነት ሥራቸዉ ወደ ዐቃቤ ሕግነት በመመለስ ስራ ከጀመሩ በኋላ የተደራጁ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነዉ ሰርተዋል፡፡ አቶ ዮሲያድ ላለፉት 12 ዓመታት ያካበቱትን ልምድ በመጠቀም በሀገራችን ሕገመንግስታዊ ሥርዓት እና ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመዋጋት በቁርጠኝነት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የትምህርት ዳራ

አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፣ የህግ ዲግሪ