ብራዚሊያቷ በፅኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣች

Brazilian Woman Sentenced to Rigorous Imprisonment and Fine

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ 23ሺ 73 ግራም የሆነውን የኮኬይን እፅ ደብቃ ለማሳለፍ ስትል በተደረገ ፍተሻ በተያዘችው ብራዚላዊት ዜጋ ላይ ክስ አቅርቦባት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ አደረገ፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ኤልዳ ሪጂና ሳንቶስ የተባለችው ብራዚላዊ ዜግነት ያላት ተከሳሽ እፆችን ለማዘዋወር የፀና ፍቃድ ሳይኖራት መነሻዋን ብራዚል ሳኦፖሎ ከተማ አድርጋ ቀጣይ ጉዞዋን ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ለማድረግ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ሲሆን በኢትዮጵያ በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር መንገድ ለትራንዚት ባረፈችበት ጊዜ በፌደራል ፖሊሶች አደገኛ እጽዋት ቁጥጥር እና ክትትል ሰራተኞች የያዘችው ሻንጣ ሲፈተሽ በውስጡ 1ሺ 76 ጥቅል ፍሬ ሲመዘን 23 ሺ 73 ግራም የሆነውን ኮኬይን እፅ ደብቃ ለማሳለፍ ስትል የተያዘች በመሆኑ በፈፀመችው እፆችን ማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባታል፡፡

ተከሳሽም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት ቀርባ ክሱ ተነቦላት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ ያለች ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልገው ባመነችው መሠረት የጠፋተኝነት ፍርድ እንዲሰጥ ጠይቋል። ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ በተከሰሰችበት ድንጋጌ ስር በዝርዝር ያመነች በመሆኑ ባመነችው መሠረት የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም ተከሳሽን ያርማል ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራል ያለውን በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

በሌላ የችሎት ውሎ ከ 14 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን የኮኬይን እፅ ይዛ የተገኘችው ናዲራ ጋብርኤላ በጽኑ እስራት ተቀጥታለች

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ 14ሺ 412 ግራም የሚመዝን የኮኬይን እፅ በተደረገ ፍተሻ በሻንጣዋ ውስጥ የተገኘባት ብራዚላዊት ዜጋ ላይ ክስ አቅርቦባት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ አደረገ፡፡

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ሚስ ናዲራ ጋብርኤላ የተባለችው ብራዚላዊ ዜግነት ያላት ተከሳሽ ልዩ ፈቃድ ሳይኖራት ሱስ በማስያዝ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እንዲሆኑ ስለሚገፋፋ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወርና በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን ኮኬይን እፅ በሻንጣዋ ውስጥ ደብቃ ለማዘዋወር በማሰብ መነሻዋን ብራዚል ሀገር ሳኦፖሎ ከተማ አድርጋ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ በቦሌ አለም ዓቀፍ አየር መንገድ ለትራንዚት ባረፈችበት ወቅት ነሀሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ ብዛቱ 533 ፍሬ ጥቅል ኮኬይን መያዟ በፍተሻ የተገኘ በመሆኑ በፈፀመችው አደገኛ እጽ ማዘዋወር ወንጀል ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባታል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት የቀረበችው ተከሳሽም ክሱ በችሎት ተነቦላት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ ያለች ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግም ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልገው ባመነችው መሠረት የጥፋተኝነት ፍርድ ይሰጥልኝ ሲል ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሿ በተከሰሰችበት ድንጋጌ ስር በዝርዝር ያመነች በመሆኑ ባመነችው መሠረት የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንድትቀጣ ሲል ወስኖባታል፡፡

የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በኢትዮጵያ ሕግ ከተመለከቱ ወንጀሎች ውስጥ ማንኛውንም ቢያደርግ የአገሪቱ ሕግ ተግባራዊ ተደርጎበት በአገራችን ሕግ መሠረት የሚቀጣ ሲሆን የኢትዮጵያ ግዛት የብሱን፣ አየሩንና የውሃ አካላቱን ያጠቃልላል።

የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ በኢትዮጵያ ሕግ ከተመለከቱ ወንጀሎች ውስጥ ማንኛውንም ቢያደርግ የአገሪቱ ሕግ ተግባራዊ ተደርጎበት በአገራችን ሕግ መሠረት የሚቀጣ ሲሆን የኢትዮጵያ ግዛት የብሱን፣ አየሩንና የውሃ አካላቱን ያጠቃልላል።

Tagged Under: Brazil • cocaine • cocaine trafficking • court • Criminal Conviction • district • drug • Drug control • drug smuggling • ethiopian law • federal • Federal High Court • fine • guilty plea • high • imprisonment • international • international drug trafficking • jurisdiction • lideta • lideta district • paulo • Rigorous Imprisonment • sao • sao paulo • Smuggling • trafficking • Transnational crime
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች