97 ሺ 355 ግራም የሚመዝን የኮኬይን እፅ ይዛ በተገኘችው ተከሳሽ ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተባት

Prosecutor Charges Suspect Found in Possession of 97,355 Grams of Cocaine

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን 97 ሺ 355 ግራም የኮኬይን እፅ ይዛ በተገኘችው ያብስራ ይብራ ላይ ክስ መሰረተባት፡፡

ተከሳሽ ያብስራ ይብራ የዋስ መብት የተከለከለች በመሆኑ በእስር ትገኛለች

የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽዋ መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከኬንያ አገር በመነሳት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ ለጊዜው ካልተለየ እና ‘’ኦዜ’’ ወይም በዋትስአፕ መተግበሪያዋ ላይ ስሙ ‘’ቦ’’ ተብሎ ከተመዘገበ ግብረ-አበርዋ ተልከው ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር መንገድ የደረሱ 2 ሻንጣዎች ከኬንያ አገር ይዛ የመጣች በማስመሰል ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር መንገድ ውስጥ ለጊዜው ያልታወቀ ግብረ-አበርዋ ሻንጣዎቹ ላይ ሀሰተኛ ታግ በመቀየር 2 ሻንጣዎች ከአየር መንገዱ የእቃ መውሰጃ ስፍራ ወስዳ ወደ ተያዘላት ሆቴል ለመሄድ በመውጣት ላይ እያለች በተደረገ ፍተሻ በሻንጣዎቹ ውስጥ ደብቃ 92 እሽግ ፍሬ ወይም 97 ሺ 355 ግራም የሚመዝን ሰዎችን ሱስ በማስያዝ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እንዲሆኑ ስለሚገፋፋ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወርና በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደ የኮኬይን እፅ ይዛ የተገኘች በመሆኑ በፈፀመችው አደገኛ እፆችን ወደ አገር ማስገባት ወንጀል ተከሳለች፡፡

ክሱ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎትም ለተከሳሽ በችሎት ክሱ ደርሷት ስለዋስትናዋ ባነሳችው ጥያቄ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ብይን በመስጠት ተከሳሽ በማረፊያ ቤት ሆና እንድትከታተል ያዘዘ ሲሆን የእምነት ክህደት ቃሏን ለመቀበል ለ ህዳር 26/2015 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ይህ ዜና ዐቃቤ ሕግ ክስ ስለመመስረቱ ብቻ የሚገልጽ ሲሆን ተከሳሽ ከፍርድ በፊት እንደ ንጹህ የመገመት መብት መርህን ያከብራል።

Tagged Under: airport • attorney • bail denial • bole • bole international airport • cocaine • Contraband • court • Criminal Charges • drug • drug smuggling • federal • Federal High Court • federal supreme court • high • indictment • international • international crime • kenya • legal counsel • lideta • narcotics • pre-trial detention • Prosecution • Prosecutor • Smuggling • supreme • trafficking
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች