የፍትሕ ሚኒስቴር በትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ላይ ከክልል ፍትሕ ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት ስራ ሀላፊዎች እና ፎካል ፐርሰኖች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል

The Ministry of Justice Discusses its Transformation Plan with Heads of Regional Justice Bureaus and Affiliated Institutions and Focal Persons

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች እና ተጠሪ ተቋማት ከተውጣጡ አመራሮች እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ፎካል ፐርሰኖች ጋር በትራንፎርሜሽናል ዕቅድ፣ በ2016 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ እና በዕቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ ሥልጠና መስጠት እና ውይይት ማድረግ ጀምሯል።

ውይይቱን በመልዕክታቸው ያስጀመሩት በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታ እና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሀን እንደተናገሩት በሕገ-መንግስታችን እውቅና ካገኙ መርሆዎች መካከል አንዱ የሆነው የግልጸኝነት እና ተጠያቂነት መርህ እንደመሆኑ መጠን ተቋማቶቻችን የሚተገብሯቸውን ተግባራት በግልጽ ማቀድ እና በታቀደው መሠረት መፈጸም አለባቸው፤ ይህ ተጠያቂነትን ለማስፈን የራሱ የሆነ ሚና አለው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ንግግራቸውን ሲቀጥሉ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅቱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ዓላማ እና ምሰሶዎችን ከግምት ያስገባ እንዲሆን በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ዕቅድ ለማዘጋጀት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና ክልል የስራ ሀላፊዎች ጋር በዚህ መልኩ ውይይት ማድረጉ ለእቅዶቹ መሳካት ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በመሆኑም በሥልጠናው እና በውይይቱ የሚገኙ ግብዓቶችን በሚገባ ቀምሮ በተቋሙ እቅድ ውስጥ በማካተት ለአፈጻጸሙ ውጤታማነት ከምታበረክቱት ሚና በተጓዳኝ ሀገር ዐቀፍ የፍትሕ ዘርፍ ሪፖርት መዘጋጀት ይችል ዘንድ ተግታችሁ ትሰሩ ዘንድ አደራ እላለው ብለዋል።

ንግግሩን ተከትሎ በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ስርዐት ማሻሻያ እና ለውጥ አመራር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኖህ ታከለ በትራንስፎርሜሽናል ፍትሕ ዕቅዱ ዙሪያ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በአሁኑ ሰዐት በቀረበው ገለጻ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ዉይይቱ ነገን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የፍትሕ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድም ቀርቦ ውይይት የሚካሄድ ይሆናል።

Tagged Under: Accountability Budget budget year plan bureaus Capacity Building Education Federal Government institutional capacity building Justice Justice Sector Reform Justice System learning Legal Reform plan policy dialogue reform Regional Regional Governments Regional Justice Bureaus sector skill development Strategic Planning Training transformation transformation plan Transparency workshop year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች