በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት የስትራቴጂክ እቅድ ፣የስትራቴጂክ አመራር እና የለውጥ አመራርን አስመልክቶ ለተቋሙ ቡድን መሪዎች ከሐምሌ 4 እስከ ሐምሌ 6 2017 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሥልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ የፍትሕ ሚኒስቴር ይዞ ከሚንቀሳቀሳቸው ምሶሶዎች አንዱ የተቋም ግንባታ ሲሆን በዚህም ሠራተኛውንና አመራሩን ማብቃት ዓላማ በማድረግ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በየዓመቱ የሥልጠና ፍላጎት ዳሰሳ በማከናወን በራስ አቅምና ከፕሮጀክት በሚገኝ ድጋፍ የተለያዩ ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱን ያወሱት ዳሬክተሩ ዛሬ የተጀመረውም ሥልጠና የዚሁ ማዕቀፍ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ዳሬክተሩ አክለውም ሥልጠናው በሶስት ዙር የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው በአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክት ድጋፍ ከተያዙ ስራዎች መካከል የስትራቴጂክ ዕቅድ፣የስትራቴጂክ አመራር እና የለውጥ አመራር እንደሆነ በመጥቀስ ፍትሕ ሚኒስቴር አሁን ላይ ምን ይመስላል ? የትኛው ደረጃ ላይ ነው
የተቀመጠው? የሚለውን ለማወቅ ሁለት አማካሪ ድርጅቶችን በመቅጠር አማካሪዎቹ ተቋሙ ያለበትን ደረጃ አጥንተው የጥናቱን ግኝት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ከወራት በፊት መገምገሙን ያወሱት ዳሬክተሩ የግምገማ ውጤቱን መሠረት በማድረግ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችሉ በሶስት ርእሰ ጉዳዮች የተዘጋጀ የሥልጠና ማቴሪያል መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዱን በመከለስ አዲስ ስትራቴጂክ እቅድ በማውጣት ላይ በመሆኑ ሰልጣኞች በዚህ ሥልጠና የምታገኙትን ዕውቀት ለስትራቴጂክ ዕቅድ በግብዓት መጠቀም እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም በተቋሙ የሚገኙ የቡድን መሪዎች በተቋሙ ውስጥ የሚደረጉ የለውጥ ስራዎችን በመምራትና በማስተባበር ትልቅ ሚና ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው የተዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ያላቸውን የስራ ድርሻ ታሳቢ በማድረግ አውስተዋል ⵗሰልጣኞች ለሥልጠናው ስኬታማነት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባቸው በአፅኖኦት ገልፀዋል፡፡
ሥልጠናውን ከቦናፋይድና ሆለስቲክ አማካሪ ድርጅት የመጡ ባለሙያዎች እየሰጡት ይገኛል፡፡