የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በ2ዐ15 በጀት ዓመት 6 ወራት ውስጥ በ769 መዛግብት ላይ ክስ መመስረቱ ተገለጸ

The Directorate of Special Crime Cases Files Charges in 769 Cases During the First Six Months of the 2015 Budget Year

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት በ769 መዝገቦች 2402 በሆኑ ተከሳሾች ላይ ሥልጣን ባላቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ክስ መስርቶ ክርክሩን በማካሄድ ላይ ሲሆን በ,228 መዛግብት ላይ 251 የሚሆኑት ተከሳሾች በፍርድ ቤት ውሳኔ ማግኘታቸውን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሪት ወሰንየለሽ አድማሱ ገለጹ፡፡

እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ ውሳኔ ካገኙት 228 መዝገቦች መካከል በ215 መዛግብት 234 የሚሆኑ ተከሳሾችን ዐቃቤ ሕግ በክርክሩ ጥፋተኛ እንዲባሉ ያደረገ ሲሆን በ13 መዛግብት 17 ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑን እንዲሁም በቀሪ 541 መዝገቦች 2151 የሚሆኑ ተከሳሾች ደግሞ በፍርድ ቤት በክርክር ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡

ዳይሬክቶሬቱ ባለፉት ስድስት ወራት በተለይም በሕግ ማስከበር ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ካከናዎናቸው ተግባራት ጋር ተያይዞ በራይድ አሽከርካሪዎች ላይ የተፈፀሙ የግድያ ወንጀሎችን በተመለከተ በ9 መዝገቦች ላይ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የምርመራ ስራ ተሰርቶ ምርመራቸው በተጠናቀቀ 6 መዝገቦች ላይ 12 ተከሳሾች በከባድ ውንብድናና በህገ-ወጥ መልኩ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ መመስረቱን እና በክርክር ሂደት ላይ መሆኑንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሪት ወሰንየለሽ አክለውም የይግባኝ ክርክርን በተመለከተም የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ባለፉት ስድስት ወራት በ41 መዝገቦች ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 6የጸና፣ 6የተሻሻለ እንዲሁም 1ተሽሮ በአጠቃላይ በ13 መዛግብት ላይ ዐቃቤ ሕግ ውሳኔ አሰጥቶ ቀሪ 28 መዛግብት ደግሞ በሂደት ላይ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የከባድ ግድያ ወንጀሎችን፣ የውንብድና እና የትራፊክ ወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የሚመጡ አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ የምርመራ ስራዎችን በጋራ በመሥራት አጥፊዎችን ወደ ሕግ የማቅረብ እና የማስጠየቅ ስራ እንደሚሰራ ወ/ት ወሰንየለሽ የተናገሩ ሲሆን በዳይሬክቶሬቱ በተለያዩ ጊዜያት በተከሳሽ አለመቅረብ ምክንያት ተቋርጠው ከነበሩ መዛግብት መካከል 7 መዝገቦች ተከሳሽን በማግኘት ወደ ክርክር እንዲገቡ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

ዳይሬክቶሬቱ ከልዩ ልዩ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ በክርከር ላይ ያሉ መዝገቦችን ውሳኔ የማሰጠት ስራዎችን እና በምርመራ ላይ ያሉ ወንጀሎችን አጠናቆ ክስ የመመስረት ሂደትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እንደሚሰራ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን ቅንጂታዊ አሠራር ማጠናከር ወ/ሪት ወሰንየለሽ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው በማለት ካስቀመጧቸው ነጥቦች መካከል ይገኙበታል፡፡

ዳይሬክተሯ በመጨረሻም የመኪና ባለንብረቶች መኪኖቻቸውን ህጋዊና የተጠናከረ ጥበቃ በሚደረግበት ሥፍራ የማቆም ልምድ ቢኖራቸው እንዲሁም እያንዳንዱን የመኪናቸውን ክፍል የሞተር፣ የሻንሲ ቁጥር ማወቅና ማስረጃዎቻቸውን በጥንቃቄ መያዝን ጨምሮ በውክልና የመኪና ሽያጭ ከሚያከናውኑ ሰዎች ዝርዝር ማጣራት ሳያደርጉ መግዛት ለችግር ይዳርጋል ብለዋል፡፡

ወ/ሪት ወሰንየለሽ ከዚሁ ጋር አያይዘው እንደምክንያት ያነሱትም በስርቆት የተገኙ መኪኖች ሽያጭን አስመልክቶ አንደኛ ገንዘባቸውን ትክክለኛ የመኪናው ባለቤት ላልሆነ፣ በሌብነት ንብረቱ ዕጁ ለገባና ህጋዊ ሻጭ መስሎ ለቀረበ ሰው በመክፈላቸው, መኪናው የተሰረቀ በመሆኑም ለትክክለኛ ባለንብረቱ ሲመለስ ለተደራራቢ ኪሳራ ከመዳረጋቸውም በላይ የተሰረቀ ንብረት በመግዛታቸው የወንጀል ተጠያቂነትን ስለሚያስከትልባቸው ማህበረሰቡ ከእንደዚህ አይነት የወንጀል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Tagged Under: acquittal • Amhara • amhara region • appeals • cases • charges • convictions • court decisions • Courts • Crime • criminal • criminal cases • Criminal Liability • directorate • federal • Fraud • high • Investigations • Legal Proceedings • police cooperation • property crime • region • special • Theft • vehicle theft
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች