የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

Six-Month Performance Review of the 2018 Fiscal Year Conducted by Attorney General Division

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የ2018 ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ጥር 1/2018 ዓ.ም ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በግምገማ መድረኩ የዘርፉ የስድስት ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በበጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት ውስጥ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ፣ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን ለህግ በማቅረብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ከማድረግ እንዲሁም በሙስና እና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች የተመዘበሩ የህዝብና የመንግስት ሐብት በማስመለስ የህዝብና የመንግስትን ጥቅም ከማስጠበቅ ረገድ ከዕቅድ አኳይ ውጤታማ እንደነበሩ ተገምግሟል፡፡

ሪፖርቱን ተከትሎ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ እና ከድሬዳዋ ፖሊስ አካላት ጋር በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት የወንጀል ምርመራ ስራዎችን በጋራ በመስራት የምርመራን ጥራት፣ በቅልጥፍና እና ውጤታማነትን ከማሻሻል ረገድ አበረታች ውጤት የተገኘበት መሆኑ፣ በሕዝብና በመንግስት ጥቅም ላይ በተፈፀሙ ከባድ ወንጀሎች የተመዘበሩ የህዝብና የመንግስት ሐብት ለማስመለስ የተሰሩ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው መሆኑን ገልፀው በተከለሰው የአምስት ዓመት የተቋሙ ስትራቴጂ መሰረት በዘርፉ እንዲከናወኑ የተያዙ ግቦችና ተግባራትን ለማሳካት በጥብቅ ዲሲፕሊን በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

Tagged Under: appeal • appropriation • attorney • Attorney General • Budget • conduct • court • division • duty • Economic • finance • financial • fiscal • Fiscal Year • general • judiciary • lawyer • legal counsel • office of the attorney general • per • performance • Performance Review • Prosecution • review • six-month • Tax • vision • year
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች