የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የተቋሙን የአገልግሎት ተጠቃሚዎችና መረጃ ፈላጊዎችን ፍላጎት መሰረት ባደረገ መልኩ በአዲስ መልኩ ያለማውን ተቋማዊ ድረ-ገፅ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
በአዲስ መልኩ የለማው ይህ ድረ-ገፅ በተለያዩ ጊዜያት የወጡ እንዲሁም ወቅታዊ የሆኑ አዋጆችንና መመሪያዎችን ያሉበትን ደረጃ ማለትም በትግበራ ላይ ያሉ እንደሆነ፣ የተሻሩ እና በከፊል የተሸሩ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ያደርጋል፤ የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጁን ተከትሎ በተቋማት የሚወጡና የተመዘገቡ መመሪያዎችን ለህዝብ ያደርሳል እንዲሁም የማህበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት ሥራችን ሰፋ በለ መልኩ ይዳስሳል፡፡
ድረ-ገፁ ተቋማዊ የሥራ ግልፀኝነትን ከማጠናከር ፤ የተጠቃሚውን አካል የሕግ ዕውቀትን ከማሻሻል እንዲሁም አለፍ ሲል የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን አኳያ የራሱ የሆነ አበርክትዎ እንደሚኖረው ተገልጹዋል፡፡
በዋናነት በድረ-ገፁ የተለያዩ አዋጆች፤ መመሪያዎችንና ዓለማቀፍ ስምምነቶችን፤ ወቅታዊ ዜናዎችና ሪፖርቶች፤ የዜና መግለጫዎችን፤ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ ፅሁፎችን፤ የተቋሙን ድርጅታዊ መዋቅር እንዲሁም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን አድራሻ፤ተለያዩ ተቋማዊ የሕትመት ውጤቶችን ፤ የመረጃ አሰሾችን ፤ ተቋማዊ ዋና ዋና ተግባራትን፣ ታሪክና አበይት ክንውኖችን፤ የኦንላይን የቅሬታ ማቅረቢያ ሥርዓትን እና መሰል ጉዳዩችን ለመረጃ ፈላላጊዎች እና ለተቋሙ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በቀላሉ ማግኘት በሚያስችል እና ግልፅ በሆነ መልቁኩ ይዞ ቀርቧል፡፡