በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Individual Charged with Rape Sentenced to Rigorous Imprisonment

ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌዉ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታዉ ኪንባ ሠፈር ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በግምት 12፡30 ሰዓት ሲሆን በ1996 ዓ/ም የወጣዉን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 626/4/ሀ/ እና 628/ሀ/ ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ልጅ ላይ በፈጸመዉ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ተከሶ ፍ/ቤት ቀርቧል፡፡

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳዉ የግል ተበዳይ ከ17 እስከ 18 ዓመት የምትሆን እና በተከሳሽ ቤት ዉስጥ በጥገኝነት የምትኖር ስትሆን ተከሳሽ ቀኑ ባልታወቀ ሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በራሱ የመኖሪያ ቤት ዉስጥ በተደጋጋሚ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈፀም ተበዳይዋ ለእርግዝና ያደረገ መሆኑ እና ቀኑ ባልታወቀ ግንቦት ወር 2014 ዓ/ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ባለዉ ጊዜ በተከሳሽ መኖሪያ ዉስጥ በተደጋጋሚ በማስፈራራት እና በማስገደድ የግብረ ስጋ ግንኙነት የፈፀመባት በመሆኑ ተከሳሽ በተበዳይ ላይ በፈጸመዉ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል የፈፀመባት በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ሕግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዳሉ ያላቸዉን 2(ሁለት) የሰዉ ምስክሮችን እና 2(ሁለት) የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ የተከራከረ ሲሆን ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ ያቀረበዉ የመከላከያ ምስክር ጥፋቱን ያላስተባበለ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ተከሳሹን ጥፋተኛ ነዉ ብሎታል፡፡

በመጨረሻም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሹን በስምንት (8)ዓመት ፅኑ እስራት እና ከህዝባዊ መብቱ ለ2 (ሁለት ዓመት) ተገድቦ እንዲቆይ በማለት ወስኖበታል፡፡

Tagged Under: Criminal Prosecution • Rape • Sentencing • sexual assault
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች