በፍትህ ሚንስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሚንስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ተስፋዬ ዳባ የተመራ የትራንስፎርሜሽን ግብረሃይል በሐረሪ ክልል የሶስት አመት የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸምን ጥር 6/2018 ዓ.ም ገምግሟል።
በግምገማ መድረኩ የሐረሪ ክልል የሶስት አመቱ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ የ2018 የ6 ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥን ተደራሽ ከማድረግና የተቀናጀ የአሰራ ስርአትን በዘመናዊ መልኩ ከመዘርጋ፤ ከየሰብአዊ መብት አያያዝ ፤ በወንጀል መከላከል፤ የህጎች ተፈጻሚነትና አተገባበርን ከመከታተል፤ በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር፤ የመንግስትና የህዝብን ጥቅም በማስጠበቅ፤ የመሰረተ ማኅበረሰብ ፍትሕ ስርዓትን ከማጠናከር፤ ባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ማቋቋምን ጨምሮ የፍትሕ ተቋማትን አቅም ከመግንባት ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ተግበራት አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ በክልሉ በፍትሕ ስርአቱ የህዝብን አመኔታን ለማትረፍ እየተሰራ ያለው ቀንጅታዊ አሰራር መጠናከር እንዳለበት በመግልፅ በክልሉ ያሉ አማራጭ የግጭት መፍቻ ስርዓቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመው፤ የ3 አመቱን የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድን በተሟላ ሁኔታ እውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ክፍተቶችን በመለየትና የተቀናጀ አሰራር ስርአትን በመዘርጋት ትኩረት ተደርጎ ሊሰራ እንደሚገባ በሰጡት ቀጣይ አቅጣጫ አመላክተዋል።
በመጨረሻም ግብረሃይሉ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበይነ መረብ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥና በክልሉ ማረሚያ ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የሰብአዊ መብት አያያዝን ጎብኝተዋል።
በግምገማ መድረኩ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፤ ፍርድ ቤቶች፤ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ማረሚያ ቤት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡