የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፍቃድ ለማግኘት ይቻል ዘንድ ፈተናው ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥና ፈተናው የሚሰጥበት ቦታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለፅ ስለመሆኑ በ23/01/2016 ዓ.ም በማስታወቂያ መነገሩ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሠረት የፈተና ኮድ የሚሰጠው ጥቅምት 01 እና 02 ቀን 2016 ዓ.ም በፍትሕ ሚኒስቴር ሲሆን ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ ደግሞ ፒያሳ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዳራሽ በመሆኑ ፈተናው ከሚጀመርበት ከጥዋቱ 3.00 በፊት በፈተናው ቦታ እንድትገኙና ከሕግ ኮዶች በስተቀር ምንም አይነት ጽሑፍ ይዞ መገኘትም የተከለከለ መሆኑን እንድታውቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡