ጠበቃና የህግ አማካሪው ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰቧቸዉን ታሪካዊ ይዘት ያላቸዉና እስከ 1990 ድርስ ያለውን የፍትሕ ስርዓት የሚያስቃኙ ፎቶ ግራፎችንና ዝርዝር መግለጫዎችን ለተቋሙ አሰረከቡ

Advocate and Legal Counsel Submit Historical Photos and Details Depicting the Justice System Up to 1990 to the Institution

ፍትሕ ሚኒስቴር በተለያዩ ዘመናት የፍትሕ ስርዓቱን ለማጎልበት ጥቅም ላይ የዋሉ ሕጎች፣ አዋጆች፣ ደንቦች፣ ዝንባሌዎችና ተግባራትን የሚያስቋኙ ታሪካዊ ሰነዶች፣ በምስልና ድምጽ የተደገፉ ማስረጃዎች፣ ከፍትሕ ስርዓቱ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ያላቸዉን ልዩ ልዩ ማስረጃዎች ከተለያዩ አካላት በማሰባሰብና በአንድ ማዕከል በማደራጀት ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ብሎም ለጥናትና ምርምር አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ተቋሙ ለዚሁ ዓላማ የሚዉል ዘመናዊ የፍትሕ ሙዚየም አስገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን የተቋሙን ጥረት ለመድገፍ በማሰብ ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት አቶ ሲሳይ ተፈራ ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰቧቸዉንና እስከ 1990 ድርስ ያለዉን የፍትሕ ስርዓት የሚያስቃኙ ታሪካዊ ይዘት ያላቸዉን ፎቶ ግራፎችንና ዝርዝር መግለጫዎችን በሃርድ ኮፒና በሲዲ አደራጅተው ለሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን በትላንትናው ዕለት ያስረከቡ ሲሆን ሌሎችም በተመሳሳይ መልኩ ድጋፋቸዉን እንዲገልጹ ጠይቀዋል፡፡

Tagged Under: documentation • Documents • Ethiopian Justice System • Evidence • historical • history • Justice • Justice System Reform • legal • legal counsel • legal history • Legal Reforms • ministry • ministry of justice (ethiopia) • proof • reforms • system • testimony
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች