በአገልግሎት ላይ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ሀሳብን በነፃ የመያዝ፣ የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነት የተረጋገጠ በመሆኑ እንዲሁም ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሀሳቦችና አመለካከቶች በነፃ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሲባል ፕሬስ በተቋምነቱ የአሰራር ነፃነትና የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ እንዲኖረው የሕግ ጥበቃ እንደሚደረግለት እና በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንደሚመራ በመደንገጉ፤

ፕሬስ ለሕዝብ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማቅረብ፣ በማስተማርና በማዝናናት እንዲሁም የዜጎችን ሀሳብን የመግለጽ ሕገ መንግስታዊ መብትን ተግባራዊ በማድረግ እና የተለያዩ አመለካከቶችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ በሕዝቦች እኩልነት እና መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት፣ ለዲሞክራሲ ስርዓት መዳበር ተፈላጊ የሆነውን የጋራ አገራዊ እምነትና አመለካከት እንዲፈጠር በማድረግ እንዲሁም ሕዝቡ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎችና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በሰፊው እንዲሳተፍ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፤

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለአገራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋፅኦ የሚያደርግ፣ ጥራቱ የተጠበቀ፣ ተወዳዳሪ፣ ተደራሽ እና ብዝሃነትን የሚያስተናግድ አስተማማኝ የፕሬስ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ሕገ መንግስታዊ ተልእኮውን በብቃት ለመወጣት በሚችልበት ሁኔታ እንደገና ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ከቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተያይዞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገና እየተሻሻለ የመጣውን የፕሬስ አገልግሎት ተግባራዊ በማድረግና ከዘርፉ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር አብሮ እንዲጓዝ በማድረግ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አደረጃጀትና አሠራር በአዲስ መልክ እንደገና ማዋቀር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ እንዲሁም፤

እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ በተሻሻለ ሕግ መተካት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1151/2011
ቀን: ነሐሴ 6፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1308/2016

የካቲት 1፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1309/2016

ታኅሣሥ 12÷ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1279/2015

የካቲት 2፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1276/2014

መስከረም 10፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1172 /2012

ታህሣሥ 8፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1115/2011

የካቲት 19፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ