በአገልግሎት ላይ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ

የአገሪቱን ልማት፣ ሠላም፣ ዲሞክራሲ እና የሕዝቦችን በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ አንድነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የዜና አገልግሎት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደ አገራዊ የዜና አገልግሎት የአገሪቱን ገፅታ ለመገንባት የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ መወጣት የሚያስችለው ተቋማዊና የአሰራር ነፃነት እንዲሁም የተሻለ የህግ ጥበቃ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የስራ ባህሪውን ባገናዘበ መንገድ እንዲመራ እና የሥራ እድገትና ቅልጥፍናው በተሻለ መንገድ እንዲራመድ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አሰራርና አደረጃጀት ከዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ እና ሙያዊ እድገት ጋር የተጣጠመ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲን እንደገና በማቋቋም ተቋሙ የሚሰጠው አገልግሎት የበለጠ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ተወዳዳሪ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ለስራና ሰራተኛ አመቺ የሆነ የስራ አካባቢን መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ዋና ዋና አገራዊ ኹነቶችንና ክስተቶችን በጽሁፍ፣ በድምፅ፣ በፎቶና ተንቀሳቃሳሽ ምስል በማስደገፍ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ስራዎች ለምርምርና ጥናት ግብዓትነት እንዲውሉ ሰንዶ የማስቀመጥ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ራሱን በገቢ መደገፍ እንዲችል ገቢ የሚያመነጭባቸው ስራዎች ላይ መሳተፍ የሚያስችለው ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግስት አንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

 

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1115/2011
ቀን: የካቲት 19፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 9/2011

ነሐሴ 8፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ