ለጅማ – ጭዳ እና ሶዶ – ሳውሳ የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 9 ቢሊዮን 655 ሚሊዮን የጃፓን የን (ዘጠኝ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት ሚሊዮን የጃፓን የን) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ መካከል መጋቢት 21 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡