የዕፅዋት አዳቃዮች መብት አዋጅ

በምርምር የተገኙ አዳዲስ የዕፅዋት ዝርያዎችን መጠቀም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ፣

አዳዲስ የዕፅዋት ዝርያዎችን በምርምር አዳቅሎ ማውጣት ከፍተኛ ጥራትና መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ፣

አዳዲስ የዕፅዋት ዝርያዎችን በምርምር አዳቅሎ በማውጣት ሥራ ላይየተሰማሩ ሰዎች በመስኩ የሚያደርጉትን ጥረትና ኢንቨስትመንት ለማበረታታት ለሥራቸው ውጤት እውቅና መስጠትና የኢኮኖሚ ጥቅም እንዲያገኙበት ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

የዕዕዋት አዳቃዮችን መብት ከማበረታታት ጐን ለጐን አዳዲስ የዕዕዋት ዝርያን በማውጣት ግብዓት የሆነውን የዕዕዋት ጀነቲክ ሀብት ጠብቀው ያቆዩትና ወደፊትም የሚጠብቁት የአገራችን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ዘርን የመጠቀምና መለዋወጥ ለዘመናት የቆየው ልማዳዊ ሥርዓታቸው እንዲቀጥል ማድረግ አስፈላጊና ተገቢ በመሆኑ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል::

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 481/1998
ቀን: የካቲት 20፥ 1998 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1288/2015

ሐምሌ 17፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1289/2015

ሰኔ 29፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 527/2015

ታኅሣሥ 4፥ 2015 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 509/2014

ሚያዝያ 15፥ 2014 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 465/2012

መጋቢት 18፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ