በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥትና በአፍሪካ ቀንድ እና የታላላቅ ሐይቆች አካባቢ አገሮች መካከል የሕገ ወጥ፣ ትናንሽና ቀላል የጦር መሣሪያዎችን ዝውውር ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስምምነት ሚያዝያ 13 ቀን 1996 በናይሮቢ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው በተዋዋይ ሀገሮች ህጐች መሠረት ስምምነቱ በ፪/፫ አገሮች መጽደቁ ከተረጋገጠ በኋላ እንደሆነ በስምምነቱ በመገለፁ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 2 ቀን 1997 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•