የጦር መሳርያዎችን፣ መለዋወጫዎቻቸውንና አካሎቻቸውን እንዲሁም ፈንጂዎችን በሕገ ወጥ መንገድ ማምረትንና ማዘዋወርን ለመከላከል የወጣውን ፕሮቶኮል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ግንቦት 23 ቀን 1993 ዓ.ም ባሳለፈው ውሳኔ ቁጥር 55/255 የተቀበለው በመሆኑ፤
ይህንኑ ፕሮቶኮል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•