የጦር መሳሪያ ቁጥጥር የሀገርንና የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ እንዲሁም የዜጎችን እና የህዝቦችን መብትና ደህንነት ለማስከበር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤
ግለሰቦች የታጠቋቸውን የጦር መሳሪያዎች የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን እድል መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በስራ ላይ ባሉ ህጎችና አሰራሮች ያልተሸፈኑ ጉዳዮችን በዝርዝር ህግ መደንገግ እና ወጥነት ያለው ስርአት መፍጠር በማስፈለጉ፣
ሀገራችን ያፀደቀቻቸውን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን የሚመለከቱ አለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማስፈፀምና አለማቀፍ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስርዓትን መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሰት አንቀጽ 51 (21) ስለ ጦር መሳሪያ አያያዝ የፌደራል መንግስት ህግ እንደሚያወጣ የተደነገገ መሆኑን በመገንዘብ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሰት አንቀጽ 55 (2) (ሸ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•