የብዝሀ ሕይወት ዓለም አቀፍ ስምምነት አባላት ጉባዔ እ.አ.አ ጥቅምት 29 ቀን 2010 በናጎያ ጃፖን ባካሄደው አሥረኛ ስብሰባ የጀነቲክ ሀብቶች አርክቦት አና ሀብቶቹን ከመጠቀም የሚገኙ ጥቅሞች ሚዛናዊና ተመጣጣኝ ተጋሪነትን ለማስጠበቅ የተደረገውን የናጎያ ፕሮቶኮል ያጸደቀው በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 21 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•