የሕንፃ ግንባታ ወይም የሕንፃ ግንባታ
ማሻሻያና የአገልግሎት ለውጥ ስራ የሕዝብ
ጤንነትና ደህንነት መጠበቅ እና የህንጻ
ተደራሽነት እና ተጠቃሚነትን ለአካል ጉዳተኞች እንዲሁም ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እና ለጠቅላላ የማህበረሰብ ክፍሎች ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ፀድቀው በትግበራ ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የህንፃ ስታንዳርዶች በሁሉም የህንፃ ግንባታዎች ላይ አስገዳጅ ሆነው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በነባሩ ሕግ በአፈፃፀም የተለዩ የመልካም
አስተዳደር ችግሮች፣ የአካል ጉዳተኞችን
ተደራሽነት በሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና
የሀብት ብክነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ግልፅና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 51/3/ መሠረት የፌደራሉ መንግስት የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀገር አቀፍ መመዘኛዎችንና መሠረታዊ የፖሊሲ መለኪያዎችን የማውጣትና የማስፈፀም ሥልጣን የተሰጠው በመሆኑ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55/1/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•