ላልተማከለ ኤሌክትሪክና መብራት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ሶስት መቶ አርባ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር. ( 347 ሚሊዮን 100 ኤስ.ዲ.አር) ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ልዩ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት
የሚከተለው ታውጀል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•