በአገልግሎት ላይ

የፌዴራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ

የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚዎችን መብት በተሻለ ሁኔታ ማስከበር፣ ጥራቱን የጠበቀና የተደራጀ የጥብቅና አገልግሎት አቅርቦት መኖር፣ እና የጥብቅና አገልግሎት የሥነ-ምግባር ደረጃን ማሳደግ የሕግ የበላይነትና ፍትሕ የማግኘት መብትን ለማስከበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የሕዝብ ጥቅምን በማስጠበቅና ፍትሕን በማስፈን ዙሪያ የተደራጀ፤ የመንግስትና የሙያተኞችን ተዋጽኦ ያማከለ የጋራ አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት የሙያ ነጻነቱ የተጠበቀ የጥብቅና አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ፤

የጥብቅና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቀጣይነትና ድርጅታዊ ዋስትና ያለው የጥብቅና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የጥብቅና ድርጅት የሚመራበትንና የሚተዳደርበትን ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

ጠበቆች በተከታታይ ሥልጠና አማካኝነት በየጊዜው ከሚወጡ አዳዲስ ሕጎች፣ የሕግ ጽንሰ-ሀሳቦች እንዲሁም ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ጋር የሚተዋወቁበትን ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

ጠበቆች በግላቸውም ሆነ በተደራጀ መልኩ መብት እና ጥቅሞቻቸውን የሚያስከብሩበትን፤

እንዲሁም እውቀት፣ ክህሎት እና ሥነ-ምግባራቸውን የሚያዳብሩበት ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

በጥብቅና አገልግሎት አስተዳደር የሚነሱ ቅሬታዎች የሚስተናገዱበትን ፍትሐዊ ሥርዓት መደንገግ በማስፈለጉ፤

 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፤

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1249/2013
ቀን: ሐምሌ 29፥ 2013 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

1362/2017

ግንቦት 12÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1356/2017

ሚያዝያ 30÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1362/2017

ግንቦት 12 ፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1362/2017

ግንቦት 12÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1356/2017

ሚያዚያ 30፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1368/2017

ሚያዝያ 2÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1368/2017

ሚያዚያ 2፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1050/2009

ነሀሴ 1፥ 2009 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 405/2009

ግንቦት 18፥ 2009 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ