የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልማት ለማፋጠንና የሕዝቦቿን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና ማስፋፋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በተጨማሪ የውጭ ባለሀብቶችን የተሳትፎ መስክ ማስፋትና ሁኔታዎችን ማመቻቸት በማስፈለጉ፤
ኢንቨስትመንት የሚመራበት ሥርዓት ግልጽና ቀልጣፋ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤ እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ በሥራ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ሕግ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•