በአገልግሎት ላይ

ለዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማፅደቅ የወጣ አዋጅ ለዘላቂ የመሬት አያያዝ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 70 ሚሊዮን 600ሺ ኤስ.ዲ.አር (ሰባ ሚልዮን ስድስት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ኅዳር 28 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል:-

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1136/2011
ቀን: ሚያዚያ 11፥ 2011 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች