ለፍትሐዊ የመሰረታዊ አገልግሎቶች ማስፋፊያ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 431 ሚሊዮን ኤስ ዲ አር (አራት መቶ ሰላሳ አንድ ሚሊዮን ኤስ ዲ አር) ተጨማሪ ብድር የሚያስገኘው ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዳር 26 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•