ለልማት ፖሊሲ ፋይናንስ ማስፈፀሚያ የሚውል 430 ሚሊዮን 100 ሺህ ኤስ.ዲ.አር (አራት መቶ ሰላሳ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የገንዘብ መጠን የሚያስገኝ የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•