ለምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር እና ክልላዊ ትስስር ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 53 ሚሊዮን
600 ሺ ኤስ.ዲ.አር (ሃምሳ ሦስት ሚልዮን ስድስት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ጥቅምት 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚያዚያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው ስብስባ ያፀደቀው በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•