በአገልግሎት ላይ

ለንግድ ሎጅስቲክስ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ብድር ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለንግድ ሎጅስቲክስ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል 110 ሚሊዮን 400 ሺ ኤስ.ዲ.አር (አንድ መቶ አስር ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በዓለም አቀፍ ልማት ማህበር መካከል መጋቢት 29 ቀን 2009 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 15 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፦

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1027/2009
ቀን: ሐምሌ 7፥ 2009 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች