ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንዲያግዝ ለሁለተኛው የኢትዮጵያ የዕድገት እና የተወዳዳሪነት የልማት ፖሊሲ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 91 ሚሊዮን 500 ሺ ኤስ.ዲ.አር (ዘጠና አንድ ሚሊዮን 5 መቶ ሺ በኤስ.ዲ.አር) ተጨማሪ ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር መካከል ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በአካሄደው መደበኛ ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•