ለተወዳዳሪነትና የስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 161 ሚሊዮን 600 ሺህ ኤስ.ዲ.አር (አንድ መቶ ስልሳ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል እ.አ.አ ሜይ 20 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•