ለመጠጥ ውሃና ሳንቴሽን ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 51 ሚሊዮን 100 ሺ ኤስ.ዲ.አር (ሃምሳ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ኤስ.ዲ.አር) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በዓለም ዐቀፍ የልማት ማኅበር መካከል እ.ኤ.አ. ኦገስት 23 ቀን 2004 በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፣
መሠረታዊ የኤኮኖሚ ዓለም ዐቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መፅደቅ ስላለባቸው፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 1997 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•