ለመቀሌ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል 1 ቢሊዮን 70 ሚሊዮን ሪንሚንቢ ዩዋን (አንድ ቢሊዮን ሰባ ሚሊዮን ሪንሚንቢ ዩዋን) ኮንሴሽናል ብድር የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ መካከል ሰኔ 6 ቀን 2010 ዓ.ም በቤጂንግ የተፈረመ በመሆኑ፤
እንዲሁም ለዚሁ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል 540 ሚሊዮን ሪንሚንቢ ዩዋን (አምስት መቶ አርባ ሚሊዮን ሪንሚንቢ ዩዋን) በቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ በኩል የሚቀርብ ከወለድ ነፃ የሆነ የማዕቀፍ የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡-
•
•
•
•
•
•