በአገልግሎት ላይ

በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀምን ማጭበርበር ለመከላከል በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በስሎቫክ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የተደረገው ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በስሎቫክ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀምን ማጭበርበር ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት መስከረም 21 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንን ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 22 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1033/2009
ቀን: ሐምሌ 5፥ 2009 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1301/2016

ታህሳስ 10፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ