ለቆጋ የመስኖ ልማትና የተፋሰስ እንክብካቤ ፕሮጀክት ማስፈ ጸሚያ የሚውል መጠኑ ዩ ኤ 32 ሚሊዮን 590ሺ 100 (ሠላሳ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሺ አንድ መቶ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ ሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እኤአ ጁላይ 19 ቀን 2001 በአቢጃን የተፈረመ በመሆኑ፡
መሠረታዊ የኢኮኖሚ ዓለም አቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆ ናቸው በፊት መፅደቅ ስላለባቸው
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሣሥ 25 ቀን 1994 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•