ለቡታጅራ ሆሳዕና ሶዶ የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈ ጸሚያ የሚውል ዩኤ 41 ሚሊዮን 310ሺ (አርባ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ አሥር ሺ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እኤአ ኖቬምበር 16 ቀን 2001 በአቢጃን የተፈረመ በመሆኑ
መሠረታዊ የኤኮኖሚ ዓለም ዓቀፍ ውሎች ተፈፃሚ ከመሆናቸው በፊት መፅደቅ ስላለባቸው፣
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 9 ቀን 1994 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፣
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•