የአርሶ አደሩን፣ ከፊል አርብቶ አደርና የአርብቶ አደሩን የኑሮ ደረጃ አገሪቱ ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊ፡ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ እድገት ጋር ለማራመድ እንዲቻል እንዲሁም አርሶ አደሩን፣ ከፊል አርብቶ አደሩና አርብቶ አደሩን በመሬት ይዞታው ላይ ያለውን የንብረት መብት ለማጠናከር የተሻሻለ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሥርዓት መዘርጋት አሰፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የከፊል አርብቶ አደርና የአርብቶ አደሩ ባህላዊ የመሬት አጠቃቀም እና አጠባበቅ ሥርዓት ጠቃሚና ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው ስለሆነ እና ኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮች የመሬት ይዞታ መብት በተመለከተ በህገ-መንግስቱ እውቅና የተሰጠው በመሆኑ፤
በዓለም አቀፍና በአህጉር ደረጃ የፈረመቻቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ እና በማስፈፀሚያ ሕግ ማስደገፍ በማስፈለጉ፤ እና የገጠር መሬት ምዝገባ መረጃን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማደራጀትና ለተጠቃሚው በአግባቡ ለማሰራጨት የሚያስችል ምቹ የሕግ ማዕቀፍ በመፍጠር፤
የባለይዞታዎችን የይዞታ ዋስትናን በማጠናከር በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና አጠቃቀም ላይ ጉልህ ለውጥ ለማምጣት፣ በመሬት ላይ የሚነሱ ግጭቶችን ለመቀነስ፣ እና መንግስት እና ተጠቃሚዎች አስተማማኝ የሆነ መረጃ የሚያገኙበትን ዘመናዊ የመሬት መረጃ ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
የተለያዩ የሀገሪቱ የሥነ ምህዳር ቀጠናዎችን ያገናዘበ ዘላቂ የገጠር መሬት አጠቃቀም ዕቅድ በማውጣትና በመተግበር የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት በመጠበቅና በማልማት ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ በማስፈለጉ፤
የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት የሚያረጋግጥና የሚያጠናክር የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አካታች ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
በኢትዮጵያ ፌድዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 (1) እና (2) (ሀ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•