በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን የደረጃዎች ሥርዓት መዘርጋት እና ጠንካራ የደረጃ ተቋም ማቋቋም እንዲሁም የደረጃ ዝግጅትን በተመለከተ ያለውን የሥልጣንና ተግባር መደራረብ ለማስወገድ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በሀገር ውስጥ የሚመረቱ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ እና ወደ ውጪ ሀገር የሚላኩ የኢትዮጵያ ደረጃ የውሳቸው ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ሂደቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን በመቆጣጠር በሰዎች፣ በእንስሳት፣ በእጽዋት እና በአካባቢ ጤናና ደህንነት፣ እንዲሁም በሀገር ጥቅም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያስከትሉ መከላከል ጠቃሚ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ዴረጃዎች ትግበራን በተመለከተ በተቆጣጣሪ አካላት መካከል የተጠናከረ ቅንጅታዊ የዴረጃዎችን ትግበራ በሚመለከት ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ደረጃዎች ዝግጅት እና አተገባበር ከዓለም አቀፍ አሰራር ጋር የተጣጣመ እንዲሆን በማድረግ፣ የኢኮኖሚ እድገት እና ማህበራዊ ለውጦችን ያገናዘበና በደረጃ ዝግጅትና ትግበራ ሂደት ያጋጠሙ የአሰራር ክፍተቶችን ሲመድፈን የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የሆነ የብሔራዊ ደረጃዎች ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•