በአገልግሎት ላይ

የሕግ እና ፍትሕ ኢንስቲቲዩት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1369/2017 ዓ.ም

የፌደራል የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ለዳኝነት እና ለፍትሕ አካላት እንደመሆኑ መጠን ተጠሪነቱን ለዳኝነት አካለ እንዲሆን በማደረግ ሥራውን በነጻነት እና በገለልተኝነት እንዲያከናውን ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ የሕግ ጥናት እና ምርምር እንዲሁም የሥልጠና አገልግሎት መስጠት እንድችሉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ተጠሪነቱ ለዳኝነት አካለ የሆነ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ስራውን በአግባቡ ለማከናወን የሚያስችል የሰው ኃይሌ እና የአሰራር አደረጃጀት ያለው የፍትሕ እና ሕግ ተቋም በማቋቋም በእውቀቱ ፣ በክህሎቱ፣ በአመለካከቱ፣ እንዲሁም በሥነ-ምግባሩ ብቁ የሆነና የተሟላ ስብዕና የለው የዳኝነት እና የፍትህ አካላት አመራር እና ሙያተኛ ማፍራት ለፍትሕ ስርዓቱ ውጤታማነት እጅግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ሕጎችን ከወቅታዊ የዓለም እና የሀገሪቱ የዕድገት ደረጃ ጋር እንደዚሁም አገራችን ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣሙ ለማድረግ እንዱሁም የዳኝነት፣ የፍትሕ አካላትና ሌሎች ከፍትሕና ሕግ ሥራ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላትን ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ ጥናትና ምርምሮችን ማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ፤

የሀገሪቱ የዳኝነት እና ፍትሕ ዘርፍ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እያሳካ ስለመሆን አለመሆኑ የሚያሳይ አስተማማኝና የተሟላ የሕግና ፍትሕ መረጃ ለመሰብሰብ እና ለማዳራጀት የሚችል በቂ የሰው ኃይሌ እና አግባብነት ያለው የአሰራር እና አደረጃጀት ሥርዓት ያለው ተቋም ማቋቋም አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የዳኝነት፣ የፍትሕ አካላት እና የሕግ ትምህርት ቤቶች የሚቀናጁበትን እንዲሁም በፍትሕ ሥርዓቱና በሕግ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የሚደረጉ የማሻሻያ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለመምራትና ለማስፈጸም የሚያስችል አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዐስ አንቀጽ(1) መሠረት የሚከተለው ታውጃል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1369/2017 ዓ.ም
ቀን: መጋቢት 10፥2017 ዓ.ም.
Law Type: proclamation

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1372/2017

ሚያዚያ 8፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1372/2017

ሚያዝያ 8÷ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1353/2016

ኅዳር 10÷ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1343/2016

ጥቅምት 16÷ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1233/2013

ግንቦት 12÷ 2013 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ