የአሰሪና ሰራተኛ፣ የአካል ጉዳተኞች ስራ ስምሪት እና የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የህግ ማዕቀፎች ላይ የምክረ-ሀሳብ አተገባባር የክትትል ግኝቶች ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ

A Consultative Forum Held on Monitoring Findings Regarding the Implementation of Recommendations on Labor, Employment of Persons with Disabilities, and Overseas Employment Legal Frameworks

በውጭ አገር ስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008፣ በሀገር ውስጥ አሰሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 እና በአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 568/2000 ህጎች አፈጻፀም ላይ ከዚህ ቀደም የተሰራውን የክትትል ሪፖርት የተመላከቱ ምክረ-ሀሳቦች አተገባባር ግኝቶች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሀን (ዶ/ር) በውይይት መድረኩ እንዳሉት የሕጎችን አፈጻጸም መከታተል፣ በተለይም እንደ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት፣ የአካል ጉዳተኞች መብት እና የሀገር ውስጥ አሰሪና ሠራተኛ ሕጎች ያሉ ዘርፎችን በሚመለከት፣ በአሁኑ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ እና ዓለም አቀፍ ትስስር አንጻር እጅግ ወቅታዊና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ተግባር ከቀላል የአሠራር ሂደት የዘለለ፣ ለሀገረ መንግሥት እና ለፍትሃዊ ማኅበረሰብ ግንባታ ቁልፍ ሚና እንዳለው ጠቁመው በተለይ ለተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ መብቶች መከበር ወሳኝ መሳሪያ እና ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በቀድሞ ክትትል ግኝት የተመላከቱ ምክረ-ሀሳቦችን መፈፃቸውን ለማረጋገጥ የተሰራው የዳግም ክትትል ሪፖርት በፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል ህጎት ተፈጻሚነት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር በዝርዝር የቀረበ ሲሆን፤ ሪፖርቱ በሶስቱም ህጎች ቀድሞ የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች የተሻሻሉትን እንዲሁም ሳይፈጸሙ የቀሩ የምክረ-ሀሳብና የሕግ ድንጋጌዎቹን በግልፅ አመላክቷል፡፡

በዚህም በአዋጆቹ የተሻለ አፈጻጸም ከታየባቸው ምክረ-ሀሳቦች መካካል ደግሞ የሰራተኞችን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ፣ በተለይም የዝቅተኛ ደመወዝ ድንጋጌዎችን ለማካተት ሞዴል የስራ ውል ማሻሻያ በከፊል መሰራቱ፣ ውጭ አገር ለመሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች የአሻራ ምርመራ ተደራሽ መሆን መቻሉ፣ ሰፊ የንቃተ ሀግ ስራ በጉዳዩ ላይ መሰራቱ፣ ሀሰተኛ ሰነድ ለመከላከል እና መረጃዎችን ለማዘመን አስፋለጊ ሲሰተሞች መልማታቸው፣ ስራ ፈላጊ አካል ጉዳተኞች የሚመዘገቡበት ስርዓት መዘጋጀቱ ይጠቀሳሉ፡፡

በተያያዘም መመሪያዎች በረቂቅ ደረጃ የሚገኙ እና ፀድቀው ወደ ስራ አለመግባታቸው፣ በውጭ አገር የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚገኙባቸው እና የመብት ጥሰት ወደሚበዛባቸው የገልፍ አገራት ዜጎች መብታቸው እንዲጠበቅ ሌበር አታሼ በሚሲዮኖች እና ቆንጽላዎች አለመመደባቸው፤ ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች የጤና ምርመራ በሚገኙበት አካባቢ ተደራሽ አለመሆኑ እና ከገልፍ ሀገራት ባሻገር ወደ ሌሎች የዓለም አህጉራት እና ሀገራት በቤት ሠራተኛነት ብቻ ሳይገደብ በተለያዩ የሙያ መስኮች ዜጎችን ለመላክ የተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶች አለመኖር በአዋጆቹ አፈፃፀም ላይ ከታዩ ውስንነቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት ናቸው፡፡

ለተነሱት ሀሳቦች የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትር ዴታው እና ስራ ክፍሉ ሃላፊ ከመድረኩ የተነሱትን ወሳኝ እና ጠቋሚ ግብአቶች በመውሰድ የዳግም ክትትሉ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን የለየ መሆኑን ጠቅሰው የተሻሻለው ሪፖርት ክትትል የተደረገበትን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ለሚቆጣጠረው የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎች እንደ ግብአት የሚወሰድ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በየውይይት መድረኩ ላይ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እንዲሁም የስራ እና የሲቪል ማህበራት የተወከሉ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

Tagged Under: Bilateral Agreements civil civil liberties disability disability employment employment employment law fundamental rights human Human Rights labor labor law law legislative legislative compliance liberties monitoring report overseas overseas employment parliamentary committee Rights wage regulations worker's worker's rights
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች

No data was found