በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አተገባባርን ለመዳሰስ እና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ጉብኝት ተካሄደ

Visit Conducted to Assess and Support the Implementation of the Transformation Plan in the Sidama National Regional State

የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ክትትል ለማድረግ በየክልሎቹ ጉብኝት የተጀመረ ሲሆን በዚሁ መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈቃዱ ፀጋ የተመራ የአመራሮች ቡድን በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሀዋሳ ከተማ ህዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም በመገኘት ውይይት እና የአካል ምልከታ አድርጓል፡፡

በውይይት ሂደቱም ከክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ ከክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ፣ ከማረሚያ ቤት ኮሚሽነር እና ሌሎች አመራሮች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን የትራንስፎርሜሽን እቅዱን በተመለከተ ክልላዊ እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ በክልሉ ፍትሕ ቢሮ ገለፃ የቀረበ ሲሆን በሂደቱም ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ በሁሉም አምድ ስር እቅድ መዘጋጀቱን፣ አፈጻጸሙን ለመከታተል በክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የሚመራ አብይ ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴ መደራጀቱን፣ በዞንና በወረዳ ጭምር ለማውረድ አደረጃጀት ተፈጥሮ እቅዱን ለማስረፅ ተከታታይ መድረኮች ተዘጋጅተዋል።

በተጨማሪም በእቅድ ከተቀመጡት ተግባራት የማኅበረሰብ ፍትሕን ከመተግበር አንጻር በክልሉ የሚተገበረውን አፈኒ የተሰኘ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት በሕግ እውቅና ለመስጠት የሕግ ረቀቅ መዘጋጀቱን፣ በክልሉ ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም ማረሚያ ቤቶች የአመራርና ባለሙያ ማጥራት ስራዎች መጀመራቸውንና በፍርድ ቤት ደረጃም በተናጠል የማጥራት ስራዎች መከናወናቸውን በቀጣይም እንደሚቀጥል ለዚህም ከሕዝብ አስተያየት መወሰዱንና የትግበራ ማኑዋል መዘጋጀቱን ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በወንጀልና በፍትሐብሄር አሠራር ስርዓትን ከማሻሻል አንጸር የተለያዩ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን፣ ሌሎች ከቅንጅታዊ አሠራርና የህብረተሰብ ተሳትፎ አንፃር እና የኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ የተጀመሩ ስራዎች ተጠቃለው ቀርበዋል፡፡

በውይይቱ በዋናነት ሁሉንም የትራንስፎርሜሽን አምዶች በነቂስ በመውሰድ ስራዎች የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶላቸው እንዲጀመሩ ከማድረግ አንፃር ትኩረት እንዲሰጥ፣ በተለይ የመሰረተ-ማኅበረሰብ የፍትሕ አገልግሎት፣ የአመራሮችና ባለሙያዎች ማጥራት ስራዎችና ስራን በቴክኖሎጂ ማዘመን ጉዳዮች ከመደበኛ ስራዎች ከፍ ባለ ደረጃ ስርነቀል ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መሰራት እንዳለባቸው አስተያየት ቀርቧል፡፡

እንዲሁም የትራንስፎርሜሽን እቅዱ ክልላዊ አደረጃጀቶች ሴቶችን ተሳትፎ እንዲያካትቱ፣ የሲቪክ ማኅበረሰብና የልማት አጋሮች እንዲሳትፉና ከፌዴራልና ሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር ያለው ቅንጅት እንዲጠናከሩ በተጨማሪም የተጠናከረ ንቃተ-ሕግ እና የሕግ ድጋፍ ትግበራን አስመልክቶ የተጀመሩት ስራዎች መጠናከርና የተጀመረው የበላይ አመራር ቁርጠኝነት መቀጠል እንዳለበት በውይይት ተነስተዋል፡፡

በመጨረሻም በፍትሕ ረገድ የሚሰሩት ስራዎች የኅብረተሰቡን አመኔታ ያተረፉ እንዲሆን ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታ ታሳቢ ተደርገው መሰራት እንደሚገባቸው ሆኖም ስርነቀል ለውጥ ማምጣትን ታሳቢ ማድረግ እንዳለባቸውና እቅዱን በማወያየት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ በተግባር መረጋገጥ እንዳለበት ተግባራቱ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ሥራዎች በመከፋፈል በዚህ በጀት ዓመት መጀመር ያለባቸው ስራዎችን እንዲጀመሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ ባለሙያና አመራር ማጥራትን በተመለከተ የተዘጋጀው ማኑዋል ሂደቱን የሚያከናውነውን አካል ገለልተኝነት እንዲያረጋግጥ፣ ምክንያተዊ መለኪያዎች እንዲኖሩት በማድረግ የተሻለ እንደሚሆን በጉብኝት ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ጸጋ መደምደሚያ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የውይይት መድረኩ እንደተጠናቀቀ ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል፤ የሚገኘውን የተቀናጀ የጾታዊ ጥቃት ምላሽ መስጫ ማዕከል እና የሲዳማ ክልል የሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ የተጎበኘ ሲሆን ከአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተገኘ ኮምፒውተርቶችና የቢሮ መገልገያ እቃዎች በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል በስጦታነት ተበርክቷል።

Tagged Under: Attorney General’s Office • Capacity Building • Civil Society • Community Justice • Courts • development partners • European Union • federal ministry of justice • hawassa city • Information technology • justice bureau • Justice Sector Transformation Plan • Law Enforcement • Legal Aid • officer • Police • Prosecution • regional high court • Rule of Law • Security • sidama • sidama national regional state • standing committee on law and justice • transformative justice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች