ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ለመቀመጥ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጲያዊት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በሕግ ዕውቅና ካገኘ የትምህርት ተቋም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች/የኢትዮጵያዊያን መሠረታዊ ሕጎች የሚያውቅና በሙያው ቢያንስ ሶስት ዓመት ልምድ ያለው /ላት/ ወይም በሕግ ዲፕሎማ የተመረቀ/ች/ እና በሙያው አምስት ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ላት/፤
2. ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የመልካም ሥነ-ምግባር ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /የምትችል/፤
3. በወንጀል ተከሶ/ሳ ያልተቀጣ/ች፤
4. የትምህርት እና የስራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ማንነቱን/ቷን የሚገልፅ መታወቂያ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ የሚያቀርብ/የምታቀርብ፤
5. ከግል መስሪያ ቤት የሚቀርብ የስራ ልምድ የመንግሥት ግብር የተከፈለበት መሆን አለበት፤
6. ማንኛውም በሌላ ቋንቋ የተሰጠ የሥራ ልምድና የስነ-ምግባር ማስረጃ በአማርኛ ተተርጉሞ መቅረብ አለበት
7. የመመዝገቢያ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ መክፈል የሚችል/የምትችል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
– የመመዝገቢያ ቀን ከመስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
– የመመዝገቢያ ቦታ ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስትር የጥብቅና ፈቃድና ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ ነው፡፡
– ኮድ መውሰጃ ቀን ከመስከረም 24 – 25/2016 ዓ.ም ነው፡፡
– ፈተና የሚሰጥበት ቀን መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል፡፡
– የፈተናው ቦታ ኮድ በሚሰጥበት ቀን ይገለፃል፡፡