በፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ እና ማስረጃ ምዘና ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው

Training on Civil Case Management and Evidence Evaluation Underway

ከፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እና ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎች በፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ እና ማስረጃ ምዘና ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናው በዋናነት የመንግሥት እና የሕዝብን ፍትሐብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሂደት ውስጥ የመንግሥት ተቋማት የፍትሐብሔር ጉዳዮችን በምን አግባብ መያዝ እንዳለባቸው ለማመላከት እንዲሁም የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ እና ማስረጃ ምዘና ብሎም ችሎት ክርክር ላይ ባለሙያዎቹ የሚናራቸው የዳበረ እውቀትና ክህሎት አስፈላጊ በመሆኑና በዚህ ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የስልጠናው ርዕስ ጉዳይ የንቃተ ህግ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ባደረገው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፣ ስልጠናው ተግባር ተኮር እና ልምድ ልውውጥ እንዲሁም ሰፊ ውይይት የሚካሄድበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ስልጠናው በዛሬ ውሎው የፍትሐሄር ስነ-ስርዓት ህግ ምንነት ዓላማዎች ፤ ጉዳያችንን ወደ ፍ/ቤት ከመውሰዳችን በፊት ምን መስራት አለብን?፤ የፍትሐብሔር ጉዳዮች አያያዝ እና የቅድመ ክስ ሂደቶች ምንነት እንዲሁም የፍትሐብሔር አቤቱታ እና የሕግ ማዕቀፎች አጠቃላይ የፍትሐብሔር ጉዳዮች ከክስ ምስረታ እስከ አፈፃፀም ያሉትን ሂደቶች እና የክርክር ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን ፤ በቀጣይ ቀናት እንዲሁ የማስረጃ ሕግ በኢትዮጲያ፤ የማስረጃ አግባብነት እና የፍትሐብሔር ሕግ በሚል የማስረጃ ሕግን ከፍትሐብሔር ሥነ-ስርዓት ሕግ አንፃር የሚዳሰስ እና በፍትሐብሔር ግዳዮች የማስረጃ ምዘናና አቀራረብ በስልጠና መድረኩ ሰፋ ብለው እንደሚዳሰሱ ተወስቷል፡፡

ስልጠናው በፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ ሲሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

Tagged Under: academic account management age and healthcare administration and control authority Capacity Building case case management case management system civil civil and political rights criminal case management Education education and training evaluation Evidence international convention on civil and political rights international covenant on civil and political rights learning management Management Training medicine and healthcare administration and control authority medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 Monitoring and Evaluation school technical and vocational education and training technical and vocational education and training (tvet) Training un valuation way
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች